ውበት (ጥበብ) በኢስላም መነጽር
ኢስላም በራሱ ውበት ነው፡ ጥበብ ነው ። አላህም ቆንጆ ነው ቆንጆ የሆኑ ነገሮቸን ይወዳል በሃዲስ ላይ ረሱላቸን እንዳሰፈሩትማለት ነው ፡ “.. إن الله جميل يحب الجمال ..” የሰው ልጅም በተፈጥሮው በውበትና በጥበብ እንዲማረክ አድርጎ ነው አላህ የፈጠረው በተቃራኒው ደግሞ ውበት የሌላቸውን ነገሮቸ ይጠላል ማለት ነው።
ውበትን (ጥበብን) በኢስላም መነጥር ስንመለከተው አካላዊ ቅርጽ ብቻ አደለም ያለው መንፈሳዊ ውበትም አለ። ለዚህም ነው ረሱል (ሰ ዐ ወ ) ሰዎቸ ሴትን ልጅ ለትዳር... የሚከጅሏት ፡ 1_ ለውበቷ 2_ ለሃብቷ 3_ ለዘሯ 4_ ለዲኗ (እምነቷ) መሆኑን ከጠቀሱ በኋላ “فاظفر بذات الدين ....” “ባለዲኗን አደራ ” ነው ያሉት ። ምክንያቱም ውበት ለብቻው ያለ እሴት፡ ያለኢማን ፡ ባዶ
ቀፎ ነውና።
ንግግርም ቢሆን ቆንጆና መጥፎ አለው “وقولوا للناس حسنى” “ለሰዎቸ መልካሙን ተናገሩ” በማለት በቁርአን ላይ የታዘዝነው ።
ግጥም ጥበብ ነው ነገር ግን ሁሉም የግጥም አይነት አይደለም ረሱላቸንም (ሰ ዐ ወ ) እንዲህ ብለዋል < متفق عليه وقبيحه قبيح حسنه حسن الشعر كالكلام > “ግጥም እንደማንኛውም አይነት ንግግር ነው ፡ጥሩው ጥሩ ሲሆን መጥፎው ደግሞ መጥፎ ነው” ።
አንድን ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ ብለን የምናስቀምጥበት ሚዛናቸን ደግሞ ኢስላም ነው አለበለዚያ ወደ አንጻራዊ ንድፈ ሃሳብ (the theory of relativity) ልናመራ ነው ይህ ደግሞ ኢስላም ወደማይፈልገው መንገድ ሊያመራን ነው ለምሳሌ፡ ሴት ልጅ ሰውነቷን ገላልጣ ለፋሸን ሾው ወይም ለዳንስ ትርኢት ራሷን መጋበዟን አንዳንዶቹ እንደ አርት ሊወስዱት ይቸላሉ በኢስላም መነጥር ግን ዝቅጠት እንጂ ሌላ አደለም ።
በጥቅሉ አንድ ሙስሊም ነኝ የሚል ሰው የአኗኗር ዘይቤው በኢስላም አስተምህሮት ላይ የተመረኮዘ መሆን አለበት በግል ህይወቴ ላይ ሃይማኖት ጣልቃ ሊገባብኝ አይገባም ማለት የ(secularism) ርእዩት እንጂ የኢስላም አደለም ኢስላም ሁሉ ነገራቸን ላይ ጣልቃ ይገባል መስገድና መጾም ብቻማ ከሆና ኢስላምን ከሌላው ሃይማኖት ምን ለየው?!
“قل إن صلاتي ونسكي ومحياي ومماتي لله رب العالمين...” “ በል ስግደቴ ፡ አምልኮቴ ፡ መኖሬም ፡ መሞቴም ለአለማቱ ጌታ አላህ ነው ” የምትለውም የቁርአን አንቀጽ መልእክት ይኸው ነው ።
አላህ ህይወታቸንን በሙሉ ለርሱ እንድናደርግ ያግዘን አሜን!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ